-46-777-0614 info@sptc.edu.et Sawla, Gofa Zone, Ethiopia
🇬🇧 English 🇪🇹 አማርኛ

Our TVET Enterprises የቴቬት ኢንተርፕራይዞቻችን

Income-generating enterprises developed and managed by SPC trainees and staff. በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኞችና ሰራተኞች የሚተዳደሩ ገቢ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች።

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ክፍል
ICT & Business

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ክፍል

  • 1. የሶፍትዌር ልማት (Software Development)
  • • ድረ
  • ገጽ ልማት፦ ለድርጅቶች፣ ለትምህርት ቤቶችና ለግል ቢዝነሶች የሚሆኑ ዘመናዊና ምላሽ ሰጪ (Responsive) ድረ
  • ገጾችን እንሰራለን።
  • • የመረጃ አያያዝ ሲስተም (Management Systems)፦ የተቋማትን አሰራር ዲጂታላይዝ የሚያደርጉ እንደ የተማሪዎች መዝገብ፣ የሰው ኃይል እና የንብረት ቁጥጥር ሲስተሞችን እናለማለን።
  • 2. የኔትወርክ ዝርጋታ (Network Installation)
  • • የአካባቢያዊ ኔትወርክ (LAN)፦ በቢሮዎችና በህንፃዎች ውስጥ ኮምፒውተሮችንና ተያያዥ መሳርያዎችን በኬብል ወይም በዋይፋይ (Wi
  • Fi) የማገናኘት ስራ እንሰራለን።
  • • የኔትወርክ ደህንነት፦ መረጃዎች እንዳይሰረቁና ኔትወርኩ ከውጭ ጥቃት የተጠበቀ እንዲሆን ፋየርዎል (Firewall) እና ሌሎች የደህንነት መተግበሪያዎችን እንጭናለን።
  • • የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፦ ለኢንተርኔትና ለውስጥ መረጃ ልውውጥ የሚሆኑ የኔትወርክ መሳርያዎችን (Routers, Switches, Racks) የመግጠምና የማዋቀር ስራ እንሰራለን።
  • 3. የጥገና አገልግሎት (Maintenance Service)
  • • የሃርድዌር ጥገና፦ የተበላሹ ኮምፒውተሮችን፣ ላፕቶፖችን፣ ፕሪንተሮችንና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎችን በባለሙያ እንጠግናለን።
  • • የሶፍትዌር ጥገና፦ የኦፕሬቲንግ ሲስተም (Windows/Linux) ጭነት፣ የቫይረስ መከላከያ (Antivirus) እና የተለያዩ የሙያ መተግበሪያዎችን እንጭናለን።
  • ለምን የእኛን አገልግሎት ይመርጣሉ?
  • • ጥራት፦ ስራዎቹ በከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎችና አሰልጣኞች የሚከናወኑ በመሆናቸው አስተማማኝ ናቸው።
  • • ቅናሽ ዋጋ፦ የኮሌጁ ኢንተርፕራይዝ በመሆኑ ዋጋችን ከግል ተቋማት እጅግ ቅናሽ ነው።
  • • ድጋፍ፦ አገልግሎት ከሰጠን በኋላ አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ በቋሚነት እንሰጣለን።
  • አድራሻ፦ በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ (SPTC) ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የICT ዘርፍ ቢሮ በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
የኮንክሪት ወንበሮች
Construction

የኮንክሪት ወንበሮች

  • የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመናፈሻና የዕረፍት ቦታ አገልግሎት
  • ኮሌጃችን የተማሪዎችንና የሰራተኞችን የዕረፍት ጊዜ ምቹ ለማድረግ በግቢው ውስጥ ማራኪ መናፈሻዎችንና የማረፊያ ቦታዎችን አዘጋጅቷል። እነዚህ የማረፊያ ወንበሮች የኮሌጁ የቲቪቲ (TVET) ኢንተርፕራይዝ ውጤቶች ሲሆኑ፣ የሚከተሉት ዋና ዋና መገለጫዎች አሏቸው፦
  • ጥንካሬና ጥራት፦ ወንበሮቹ ከጥሩ ኮንክሪትና ከአርማታ ብረት የተሠሩ በመሆናቸው ለማንኛውም የአየር ንብረት የማይበገሩና ለረጅም ዘመናት የሚያገለግሉ ናቸው።
  • ተግባራዊ ልምምድ፦ እነዚህ ወንበሮች በህንጻ ግንባታ (Building Construction) ዘርፍ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሩትን ዕውቀት በተግባር ያሳዩባቸው ውጤቶች ናቸው።
  • ምቹ አካባቢ፦ ተማሪዎች ከትምህርት ክፍለ
  • ጊዜ በኋላ ጥላ ባላቸው ዛፎች ስር አረፍ ብለው እንዲያጠኑና እንዲወያዩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ።
  • የሽያጭ አገልግሎት፦ ኢንተርፕራይዛችን እንዲህ ያሉ ውብና ጠንካራ የሲሚንቶ ወንበሮችን ለግለሰቦች፣ ለሆቴሎችና ለድርጅቶች በተመጣጣኝ ዋጋ አምርቶ ያቀርባል።
  • አድራሻ፦ በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ።
  • SPTC
  • ክህሎትን ለውጤታማነት!
ብሎኬት  አቅርቦት
Construction

ብሎኬት አቅርቦት

  • 1. የምርቱ ጥራትና ደረጃ
  • ጥንካሬ፦ ብሎኬቶቻችን የሚመረቱት ደረጃውን የጠበቀ የሲሚንቶ፣ የአሸዋና የጠጠር ድብልቅን በመጠቀም ሲሆን፣ ለህንፃ ግንባታ አስተማማኝ ጥንካሬ አላቸው።
  • ትክክለኛ ቅርፅ፦ ዘመናዊ የብሎኬት ማምረቻ ማሽኖችን የምንጠቀም በመሆኑ፣ ብሎኬቶቹ ወጥ የሆነ መጠንና ቅርፅ አላቸው፤ ይህም ለግንባታ ስራ ምቹ ያደርጋቸዋል።
  • 2. ለምን የኮሌጁን ብሎኬት መግዛት ያስፈልጋል?
  • ተመጣጣኝ ዋጋ፦ የኮሌጁ ኢንተርፕራይዝ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠትን ቅድሚያ ስለሚሰጥ፣ ዋጋችን ከግል አምራቾች ጋር ሲወዳደር እጅግ ቅናሽ ነው።
  • የባለሙያ ክትትል፦ ምርቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞችና ባለሙያዎች የቅርብ ክትትል ስለሚመረት ጥራቱ የተረጋገጠ ነው።
  • የተግባር ልምምድ፦ ይህ የምርት ሂደት ለተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሩትን የህንፃ ግንባታ ትምህርት በተግባር እንዲለማመዱ ትልቅ እድል ይፈጥራል።
  • 3. የማህበረሰብ ተጠቃሚነት
  • ለግል ቤት ግንባታ፣ ለድርጅቶችና ለኮንስትራክሽን ስራዎች በጅምላና በችርቻሮ እናቀርባለን።
  • የኮሌጃችንን ብሎኬት በመግዛትዎ ተቋሙ ራሱን በገቢ እንዲችልና የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲያጠናክር ድጋፍ ያደርጋሉ።
  • አድራሻ፦ በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ (SPTC) ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ምርቶች ማምረቻ ማዕከል በመምጣት ምርቱን መግዛት ወይም ትዕዛዝ መስጠት ይችላሉ።
ቀይስር አቅርቦት
Manufacturing

ቀይስር አቅርቦት

  • የምርቱ ጥራትና ተፈጥሯዊነት
  • ኦርጋኒክ ምርት፦ በኮሌጁ የአትክልት ቦታዎች ላይ የሚመረት በመሆኑ፣ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን (Compost) በመጠቀም እንዲያድግ ይደረጋል።
  • ትኩስነት፦ ምርቱ በቀጥታ ከአፈር እንደወጣ ለገበያ ስለሚቀርብ፣ ተፈጥሯዊ ጣዕሙንና በውስጡ የያዛቸውን እንደ ብረት (Iron) እና ቪታሚን ያሉ ንጥረ ነገሮችን ሳይቀንስ ለተጠቃሚው ይደርሳል።
  • 2. የአቅርቦትና የዋጋ ሁኔታ
  • ተመጣጣኝ ዋጋ፦ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ባገናዘበ መልኩ ከውጭ ገበያ በረከሰ ዋጋ በግቢው ውስጥ ለሽያጭ ይቀርባል።
  • ቀጣይነት ያለው ምርት፦ ዘመናዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም በሁሉም ወቅቶች ቀይ ስርን ለገበያ የማቅረብ አቅም ተፈጥሯል።
ዶሮ እርባታ አቅርቦት
Manufacturing

ዶሮ እርባታ አቅርቦት

  • የእንቁላል ምርት፦ ትኩስ እና ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ እንቁላሎችን በየቀኑ ለገበያ እናቀርባለን።
  • ለሥጋ የሚሆኑ ዶሮዎች፦ በጤናማ ሁኔታ ያደጉ እና ጥራታቸው የተጠበቀ የሥጋ ዶሮዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን።
  • የጫጩት ሽያጭ፦ በራስዎ ማርባት ለሚፈልጉ የአካባቢው ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች ምርጥ ዝርያ ያላቸውን ጫጩቶች እናቀርባለን።
የካፌቴሪያው ዋና ዋና አገልግሎቶች
Manufacturing

የካፌቴሪያው ዋና ዋና አገልግሎቶች

  • የቁርስ አገልግሎት፦ ጠዋት ለስራና ለትምህርት ለሚመጡ ተማሪዎችና ሰራተኞች የተለያዩ የቁርስ አይነቶች በወቅቱ ይዘጋጃሉ።
  • የምሳ አገልግሎት፦ በኢትዮጵያዊ የቤት ውስጥ ጣዕም የተዘጋጁ የምሳ አማራጮች በየቀኑ ይቀርባሉ።
  • ሻይና ቡና፦ ለማህበራዊ ግንኙነትና ለዕረፍት ጊዜ የሚሆኑ ትኩስ መጠጦች ሁልጊዜም ይገኛሉ።
  • ተመጣጣኝ ዋጋ፦ ካፌው የኮሌጁ የገቢ ማስገኛ ኢንተርፕራይዝ አካል በመሆኑ፣ ዋጋው የተማሪዎችንና የሰራተኞችን አቅም ያገናዘበ ነው።
  • ምቹ ቦታ፦ በግቢው ውስጥ ለተጠቃሚዎች ምቹ በሆነ ስፍራ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለቆይታ እጅግ አመቺ ነው።
የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወፍጮ ቤት
Manufacturing

የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወፍጮ ቤት

  • ሁለንተናዊ አገልግሎት፦ በቆሎን ጨምሮ ማንኛውንም የእህል አይነት በጥራት እንፈጫለን።
  • የማይቋረጥ ስራ፦ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀናት ሁልጊዜም ለናንተ ክፍት ነን።
  • ዘመናዊ መፍጫ፦ የእህሉን ጣዕም ሳይቀይር በንፅህና እና በፍጥነት የሚያደርስ ማሽን።
  • ተመጣጣኝ ዋጋ፦ ለህብረተሰቡ ምቹ የሆነና የሁሉንም አቅም ያገናዘበ የአገልግሎት ክፍያ።
  • አድራሻችን፦ በኮሌጃችን ቅጥር ግቢ ውስጥ፤ በማንኛውም ሰዓት መጥተው ይጠቀሙ!
× Preview