-46-777-0614 info@sptc.edu.et Sawla, Gofa Zone, Ethiopia
🇬🇧 English 🇪🇹 አማርኛ

በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወደ ላቀ የትምህርት ጥራትና ብቃት የምናደርገውን ጉዞ አጠናክረናል!!!


በቀን 08/12/2018 ዓ.ም በኮሌጃችን በISO 21001:20125 የትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ስርዓት (EOMS) ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የግንዛቤ ፈጠራ መርሃ ግብር መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡ መርሃ ግብሩ የISO 21001:2025 መስፈርቶችን ከመረዳት ባለፈ፣ የጥራት አስተሳሰብን በየቀኑ በምንሠራው ሥራ እንዴት ማስረጽ እንደምንችል ያስገነዘበ ነበር። በመድረኩ የISO ምንነትና የISO 21001:2025 ዓላማ ከመገንዘብ ጀምሮ፣ የኮሌጃችን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች እና የጥራት ፖሊሲ በተግባር እንዴት ሊተረጎሙ እንደሚችሉ ተዳሷል።
በተጨማሪም አቅራቢው የISO 21001:2025 ሁሉንም ኦዲት ሊደረግባቸው የሚችሉ መስፈርቶች (Auditable Clauses) በማብራራት፣ እያንዳንዱ መስፈርት በኮሌጁ ውስጥ በተግባር፣ በማስረጃ እና በተጠያቂነት እንዴት መደገፍ እንዳለበት ግንዛቤ ሰጥቷል።
በዚህ መድረክ ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ ጊንዳ ባሕሩ ያካፈሉት መልዕክትም የጥራት ጉዞአችን የአንድ ክፍል ወይም የአንድ ግለሰብ ኃላፊነት ሳይሆን፣ የሁላችንም የጋራ ተሳትፎና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን የሚያጎላ ነበር። የተቋሙን ተልዕኮና ራዕይ በተግባር ለማሳካት እያንዳንዱ ሠራተኛ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑም ተጠናክሮ ተገልጿል።እያንዳንዱ ሠራተኛ በሚሠራው ሥራ፣ በሚሰጠው አገልግሎት፣ በሚያበረክተው ሀሳብ እና በሚያደርገው ቀጣይ መሻሻል ለኮሌጃችን ጥራት ወሳኝ አሻራ ያሳርፋል።
ISO 21001:2025 ማለት ሰርተፊኬት ብቻ አይደለም፤ ጥራትን ከፖሊሲ ወደ ተግባር፣ ከሰነድ ወደ ባህል የምንቀይርበት የልማት ጉዞ ነው።
አንድ የጋራ ራዕይ፣ አንድ የጋራ ኃላፊነት፣ አንድ የጋራ ጥራት!
“ለክህሎት ልህቀት እንተጋለን!”
#ISO21001:2025 #QualityCulture #ContinuousImprovement #EducationalQuality #SawlaPolytechnicCollege