እንኳን ደስ አለን/አላችሁ የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና ያጠናቀቁትን ሰልጣኞችን ለ16ኛ ዙር ነሃሴ 23/12/2018 ዓ.ም አስመረቀ
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ፣ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ምናሴ ኤልያስን ጨምሮ የኮሌጁ ዲን አቶ ጊንዳ ባህሩ፣ የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት፣ ተመራቂ ሰልጣኞችና ወላጆቻቸው በተገኙበት ተካሄደ ።
ሰልጣኞች በቆዩበት ጊዜ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችም የዕውቅና ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተሰጠ። ቴክኒክ ሙያ ስልጠና ሰልጣኞችን በተግባራዊ ዕውቀትና ክህሎት በማብቃት የሥራ ፈጠራን፣ ራስን መቻልንና ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። በዚህም የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኞችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማሰልጠን ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እያደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።