Latest News
News
እንኳን ደስ አለን/አላችሁ የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና ያጠናቀቁትን ሰልጣኞችን ለ16ኛ ዙር ነሃሴ 23/12/2018 ዓ.ም አስመረቀ
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ፣ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ...
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ፣ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ምናሴ ኤልያስን ጨምሮ የኮሌጁ ዲን አቶ ጊንዳ ባህሩ፣ የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት፣ ተመራቂ ሰልጣኞችና ወላጆቻቸው በተገኙበት ተካሄደ ።
ሰልጣኞች በቆዩበት ጊዜ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችም የዕውቅና ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተሰጠ። ቴክኒክ ሙያ ስልጠና ሰልጣኞችን በተግባራዊ ዕውቀትና ክህሎት በማብቃት የሥራ ፈጠራን፣ ራስን መቻልንና ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። በዚህም የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኞችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማሰልጠን ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እያደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
News
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! 2018 ዓ.ም ተመራቂዎች
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
አንጋፋው ሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 ዓ.ም ሠልጣኞችን በቀን 23/12/2018 ዓ.ም ያስመርቃል
News
በቀን 11/12/2018 ዓ.ም በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025-የትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ሥርዓት መደበኛ የውስጥ ኦዲት የመክፈቻ ስብሰባ ተካሂዷል።
በቀን 11/12/2018 ዓ.ም በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025-የትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ሥርዓት መደበኛ የውስጥ ኦዲት የመክፈቻ ስብሰባ...
በቀን 11/12/2018 ዓ.ም በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025-የትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ሥርዓት መደበኛ የውስጥ ኦዲት የመክፈቻ ስብሰባ ተካሂዷል።
ይህ ኦዲት ቀደም ሲል ከተካሄደው የመጀመሪያ/መደበኛ ያልሆነ የግምገማ ኦዲት በኋላ እና ቀጣዩን የውጭ ወይም የሶስተኛ ወገን ኦዲት (Third-Party Audit) ለመቀበል ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ የሚያገለግል ወሳኝ የዝግጅት ምዕራፍ ነው።
በዚህ ሂደት የኮሌጁ የትምህርት ተቋማት አስተዳደር ሥርዓት ከISO 21001:2025 መስፈርቶች ጋር ያለው ተጣጣሚነት ይገመገማል፣ ጠንካራ ጎኖች ይለያሉ፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮችም በመለየት ለቀጣዩ የሶስተኛ ወገን ኦዲት ዝግጅት ይደረጋል። ይህ ሂደት የኮሌጁን የጥራት ባህል ለማጠናከር፣ ተቋማዊ አሠራሮችን ለማሻሻል እና ለቀጣይነት ያለው መሻሻል ያለንን ቁርጠኝነት ለማሳየት ትልቅ እርምጃ ነው።
ለኮሌጁ አመራር፣ ለሠራተኞች እና ለኦዲት ቡድኑ ላሳዩት ትብብር፣ ቁርጠኝነት እና ለጥራት ማሻሻያ ላደረጉት ጥረት ከልብ ምስጋና እናቀርባለን።
“ለክህሎት ልህቀት እንተጋለን!”
Today, Sawla Polytechnic College held the opening meeting for the formal internal audit of ISO 21001:2025-Educational Organizations Management Systems.
This internal audit is an important stage in our ISO 21001:2025 journey, following the informal/pre-assessment audit and preceding the upcoming external (third-party) audit. It provides an opportunity to assess our Educational Organization Management System against the requirements of ISO 21001:2025, identify strengths, address areas for improvement, and strengthen our readiness for the external audit. This process demonstrates our continued commitment to quality education, effective institutional management, accountability, and continual improvement.
We sincerely appreciate the commitment, cooperation, and dedication of the college leadership, staff, and audit team as we continue working together toward a stronger culture of quality and excellence.
“We Strive for Skill Excellences!”
#SawlaPolytechnicCollege #ISO21001:2025 #InternalAudit #QualityAssurance #TVET
News
በሳውላ ፖሊቴክኒክ ተመርቶ ፤ለሳውላ ከተማ ውበት የዋለ!
ከተማችን ሳውላ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ውብ የእግረኛ መንገድ እና የጎዳና ላይ መብራቶች ተገጥመውላት ይበልጥ እየተዋበች ትገኛለች። የእኛ ሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮ...
ከተማችን ሳውላ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ውብ የእግረኛ መንገድ እና የጎዳና ላይ መብራቶች ተገጥመውላት ይበልጥ እየተዋበች ትገኛለች። የእኛ ሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለዚህ ታላቅ የከተማዋ ልማት ቀጥተኛ አስተዋጽኦ በማድረጉ ትልቅ ኩራት ይሰማዋል። በኮሌጃችን ቴክኒካል ቡድን እና አሰልጣኞች ጥራታቸውን ጠብቀው የተመረቱት የኮሪደር የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች (poles) በአሁኑ ወቅት የከተማችንን መንገድ እያደመቁ ይገኛሉ።
ይህ ስኬት ኮሌጃችን የተግባር ስልጠናን፣ የኢንጂነሪንግ ብቃትን እና ከማህበረሰቡ ጎን መቆምን በተግባር ያረጋገጠበት ነው። እኛ ቴክኖሎጂን ማስተማር ብቻ ሳይሆን ከተማችንንም እንገነባለን!
አብረን ለሳውላ ብሩህ ተስፋ እንገነባለን!
#SawlaPolytechnic #CorridorDevelopment #SawlaCity #VocationalExcellence #CommunityImpact
News
በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወደ ላቀ የትምህርት ጥራትና ብቃት የምናደርገውን ጉዞ አጠናክረናል!!!
በቀን 08/12/2018 ዓ.ም በኮሌጃችን በISO 21001:20125 የትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ስርዓት (EOMS) ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የግንዛቤ ፈጠ...
በቀን 08/12/2018 ዓ.ም በኮሌጃችን በISO 21001:20125 የትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ስርዓት (EOMS) ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የግንዛቤ ፈጠራ መርሃ ግብር መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡ መርሃ ግብሩ የISO 21001:2025 መስፈርቶችን ከመረዳት ባለፈ፣ የጥራት አስተሳሰብን በየቀኑ በምንሠራው ሥራ እንዴት ማስረጽ እንደምንችል ያስገነዘበ ነበር። በመድረኩ የISO ምንነትና የISO 21001:2025 ዓላማ ከመገንዘብ ጀምሮ፣ የኮሌጃችን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች እና የጥራት ፖሊሲ በተግባር እንዴት ሊተረጎሙ እንደሚችሉ ተዳሷል።
በተጨማሪም አቅራቢው የISO 21001:2025 ሁሉንም ኦዲት ሊደረግባቸው የሚችሉ መስፈርቶች (Auditable Clauses) በማብራራት፣ እያንዳንዱ መስፈርት በኮሌጁ ውስጥ በተግባር፣ በማስረጃ እና በተጠያቂነት እንዴት መደገፍ እንዳለበት ግንዛቤ ሰጥቷል።
በዚህ መድረክ ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ ጊንዳ ባሕሩ ያካፈሉት መልዕክትም የጥራት ጉዞአችን የአንድ ክፍል ወይም የአንድ ግለሰብ ኃላፊነት ሳይሆን፣ የሁላችንም የጋራ ተሳትፎና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን የሚያጎላ ነበር። የተቋሙን ተልዕኮና ራዕይ በተግባር ለማሳካት እያንዳንዱ ሠራተኛ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑም ተጠናክሮ ተገልጿል።እያንዳንዱ ሠራተኛ በሚሠራው ሥራ፣ በሚሰጠው አገልግሎት፣ በሚያበረክተው ሀሳብ እና በሚያደርገው ቀጣይ መሻሻል ለኮሌጃችን ጥራት ወሳኝ አሻራ ያሳርፋል።
ISO 21001:2025 ማለት ሰርተፊኬት ብቻ አይደለም፤ ጥራትን ከፖሊሲ ወደ ተግባር፣ ከሰነድ ወደ ባህል የምንቀይርበት የልማት ጉዞ ነው።
አንድ የጋራ ራዕይ፣ አንድ የጋራ ኃላፊነት፣ አንድ የጋራ ጥራት!
“ለክህሎት ልህቀት እንተጋለን!”
#ISO21001:2025 #QualityCulture #ContinuousImprovement #EducationalQuality #SawlaPolytechnicCollege
News
የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የክላስተር ኮሌጆች የቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር እና የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡
(ሳውላ፣ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም)
ሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ጋር በመተባበር “በቴክኖሎጂ እንቅደም ወደ ስኬት እንድረስ” በሚል መሪ ቃል ያዘ...
(ሳውላ፣ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም)
ሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ጋር በመተባበር “በቴክኖሎጂ እንቅደም ወደ ስኬት እንድረስ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር እና የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በደማቅ ሁኔታ ተካሂዶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ጊንዳ ባህሩ በንግግራቸው እንደገለጹት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዋና ተልዕኮ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ማፍራት፣ ተግባራዊ የምርምር ውጤቶችን ማመንጨት እና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ፈጠራዎችን ማበረታታት በመሆኑ፣ ይህ ውድድርና ኤግዚቢሽን የኮሌጆችን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳየትና የልምድ ልውውጥን ለማጠናከር አስፈላጊ መድረክ መሆኑን ገልጸው ፕሮግራሙን በይፋ ከፍተዋል።
የፕሮግራሙ ዓላማ በክላስተር ኮሌጆች ውስጥ የሚገኙ አሠልጣኞች፣ ተማሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች ያፈሯቸውን ፈጠራዊ ቴክኖሎጂዎች፣ ተግባራዊ የምርምር ውጤቶች እና ችግር ፈቺ ሥራዎችን ለማስተዋወቅ፣ የልምድ ልውውጥን ለማጎልበት እና የፈጠራ ባህልን ለማጠናከር ነበር።
በውድድሩ እና ኤግዚቢሽኑ ላይ ከተለያዩ ክላስተር ኮሌጆች የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች እና የምርምር ሥራዎች በዳኞች በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት ተገምግመው አሸናፊዎች ተለይተዋል። የቀረቡት ሥራዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራን፣ ተግባራዊነትን እና ለማህበረሰቡ ችግር መፍትሔ የመስጠት አቅማቸውን በግልጽ ሁኔታ አሳይተዋል።
በመዝጊያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ እና የኮሌጁ ምክትል ዲን ተወካይ አቶ መሳይ ባህሩ ባደረጉት ንግግር፣ በፕሮግራሙ የታዩ ፈጠራዎችና የምርምር ውጤቶች የኮሌጆችን እየተሻሻለ የመጣ የቴክኖሎጂ አቅም እንደሚያሳዩ ገልጸው፣ ወደፊትም ተቋማት በጋራ በመሥራት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማፍራትና ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ለፕሮግራሙ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ክላስተር ኮሌጆች፣ አሠልጣኞች፣ ዳኞች፣ አጋር አካላት እና የኮሌጁ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበው ፕሮግራሙን በይፋ ዘግተዋል።
Website: https://www.sptc.edu.et/
Facebook: Sawla Polytechnic